አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡለትን ሹመቶች አጽድቋል፡፡
በዚሁ መሰረት
1ኛ. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣
2ኛ. አቶ አሰግደዉ ኃ/ጊዮርጊስ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ፣
3ኛ. አቶ ሰለሞን ዲባባ – የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለ2018 ዓ.ም 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በፌደራል መንግስት ለተሰጠ የደመወዝ ድጎማ እንዲሁም 996 ሚሊየን ብሩ ለከተማዋ የልማት ሥራዎች የሚውል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው በጥቅሉ 9 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡