የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ

By sosina alemayehu

May 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ሊ ጁን ሁዋን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የዘላቂ ልማት ግቦችን አፈጻጸም ለማፋጠንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ መክረዋል።

ከፈረንጆቹ 2030 በኋላ ያለውን ዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳ በመቅረጽ ሂደት ውስጥ አፍሪካ ያላትን ድምፅ ማጠናከር በውይይቱ የተነሳ ሌላኛው አጀንዳ ነው።