አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን የሚጠበቅበትን ሚና ይወጣል አሉ የፓርቲው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)።
ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት፣ በሀገራዊና ቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያፀና መሠረት መሆኑን ገልጸው፥ የሀገር ዘላቂ ልማትና ሰላም የፓርቲው ቀዳሚ አጀንዳዎች መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
አብን ለመጪው ምርጫ የፖሊሲ አማራጮቹን ለህዝቡ እያስተዋወቀ ሲሆን፥ በዛሬው መድረክ ፓርቲው በምርጫና ድህረ ምርጫ ጉዳዮች ላይ የሚኖረውን ሚና በተመለከተ ውይይት ተደርጓል፡፡
ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት እንዲረጋገጥና መጪው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን ፓርቲው የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡
በግዛቸው ግርማዬ