የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

May 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተገናኝተን በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎በውይይቱ ወቅት ለነበራቸው ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋና አቅርበዋል።