ጤና

የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በአፋር ክልል…

By Adimasu Aragawu

May 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ በጤናው ዘርፍ የተቀናጀ ሥራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በትምህርት ቤቶች ላይ የሚካሄደው የጤና ዘመቻ መርሐ ግብር የተማሪዎችን ጤና ለማሻሻል እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሐቢብ በበኩላቸው ዘመቻው በክልሉ 11 ወረዳዎች ለሚቀጥሉት ቀናት እንደሚካሄድ አንስተው÷ ትምህርት ቤቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች መፍለቂያ በመሆናቸው የተማሪዎችን ጤና መሠረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተቀናጀ መልኩ የሚሰራው የጤና ዘመቻ በትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ጤና ከማሻሻል አኳያ ጉልህ ሚና እንዳለው የገለጹት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሣ አደም ናቸው።

መርሐ ግብሩ ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሚከናወን ተመላክቷል።

በከሊፋ ከድር