አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ በተካሄደ የራባት ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በበላይነት አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች ምድብ አትሌት ቦኪ ዲሪባ 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል፡፡
አትሌት ቶልቻ ተፈራ 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ በመግባት 2ኛ እንዲሁም አትሌት ጫሉ ዴሶ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡
በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት አለምፀሐይ አሰፋ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ3 ሴኮንድ ላይ በመግባት ውድድሯን በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡
አትሌት መሰረት አበባየው እና አትሌት ስራነሽ ይርጋ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡
አትሌት ጌጤ ጁካለ 5ኛ እንዲሁም አትሌት ኩሊ ጪምዴሳ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡