ፋና ስብስብ

የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

By sosina alemayehu

May 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በግብርና ሚኒስቴር ከ1968–1970 ዓ.ም እና ከ1983 – 1984 ዓ.ም በሚኒስትርነት አገልግለዋል።

እንዲሁም የመሬት ለአራሹ አዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ድርሻም አበርክተዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡