የሀገር ውስጥ ዜና

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሊሙ ገነት ከተማ ተጀመረ

By Yonas Getnet

May 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዞን ሊሙ ገነት ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀምሯል።

አገልግሎቱ በተጀመረበት ወቅት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ እንዳሉት ፥ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ወረዳዎች እና ታዳጊ ከተማዎች ለማስፋፋት እየተሰራ ነው።

ይህም መንግሥት በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ትጃኒ ናስር በበኩላቸው ፥ አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ በሕብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑን ጠቁመዋል።

የሊሙ ገነት ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በ8 መስኮቶች 87 የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ከ150 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በተገነባ ሕንጻ ውስጥ ከተጀመረው አገልግሎቱ በተጨማሪ በጅማ ዞን ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

በአብዱረህማን መሀመድ