የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

By Hailemaryam Tegegn

May 12, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ አቶ ዘገየ አስፋው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በግፍ የተነጠቁት መሬት እንዲመለስላቸውና የመሬት ሥሪት እንዲቀየር ግንባር ቀደም ሚና እንደነበራቸው አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት ሀገራቸውን በሚኒስትርነት ማገልገላቸውን አስታውሰዋል፡፡

ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የሀገራችንን ነባር ችግሮች በምክክር ለመፍታት በተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ሲያገለገሉ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ዘገየ እጅ አጠሮችን በመደገፍ እድሜያቸውን ሙሉ ሀገራቸውን ያገለገሉ ብርቱ አባት ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በማረፋቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል፡፡