የሀገር ውስጥ ዜና

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ

By Adimasu Aragawu

May 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ብለዋል። ‎ ‎በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝትዎ በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም አመልክተዋል።

‎ወሳኝ እና ፍሬያማ በሆኑ ውይይቶች ላይ ትኩረት በምናደርግበት በዚህ ወቅት አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ እርሱም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።