አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረጉ ቁልፍ ስምምነቶች ልውውጥን በጋራ መምራታቸውን ገልጸዋል።
በዚሁም የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት እና የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ ይገኙበታል ነው ያሉት።