የሀገር ውስጥ ዜና

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

May 14, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ ወገኖች ውይይት የተደረገው ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ “ፅናት፣ ፈጠራ፣ ትብብር እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ይገኛል።