ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የአውሮፕላን ትርኢት አካሄደ

By Adimasu Aragawu

May 14, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ልዩ የአውሮፕላን ትርኢት አካሂዷል።

አውሮፕላኖች ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡበትን ትርኢት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አስጀምረውታል።

መርሐ ግብሩ የአየር መንገዱን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከደንበኞቹና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ለማክበር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለፉትን 80 ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ ሀገራትንና ባህሎችን በማገናኘት ረገድ ያለውን ሚና እና የሰጠውን አገልግሎት ለማክበር ያለመ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀምና በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ በመሆን ሀገራትን በማቀራረብና በዓለም አቀፍ የባህልና የንግድ ልውውጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ሲጫወት ቆይቷል።

በመሳፍንት ብርሌ