የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቋቋም አስችሏል – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

By Yonas Getnet

May 15, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚሰጠው መረጃ ትክክለኛነት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቋቋም አስችሏል አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)።

የበልግ ወቅት ትንበያ ግምገማ እንዲሁም የመጪው ክረምት ወቅት ትንበያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እንዳሉት ፥ የኢንስቲትዩት የቅድመ ትንበያ መረጃ ትክክለኛነት 90 በመቶ ደርሷል።

ይህም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቋቋም እንዳስቻለ አንስተው፤ የኢንስቲትዩቱ የማስፈፀም አቅምና የመረጃ ጥራት አድጓል ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የበልግ ወቅት የተሰጠው የአየር ሁኔታ ትንበያ እና የነበረው የአየር ሁኔታ የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማዕከላትን በማጠናከር እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትክክለኛ እና ታማኝ መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

በቅድስት አባተ