አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጀርመን መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርዝ ኢራን በአፋጣኝ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት አለባት አሉ።
ፍሬድሪክ ሜርዝ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገልጸው፥ በውይይታቸውም ኢራን ወደ ድርድር መመለስ እንዳለባት መግባባታቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ባለቤት ልትሆን እንደማይገባ ተስማምተናል ነው ያሉት፡፡
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መክፈት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተው ማሳሰባቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
ኢራን ጠላት ከምትላቸው ሀገራት ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች በሰርጡ ማለፍ እንደማይችሉና ለወዳጅ ሀገራት መርከቦች ብቻ ክፍት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አባስ አራግቺ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በዮናስ ጌትነት