አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሲ ዞን የሄጦሳ ወረዳ ነዋሪዎች ሀገርን ያሻግራል፣ ለልማትና ለዜጎች እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጀተናል አሉ፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎቹ፤ የድምጽ መስጫውን ቀን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሀገርን የሚያሻግር፣ ለልማትና ለዜጎች እድገት ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፤ ምርጫው ተዓማኒ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የምርጫ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ መታዘባቸውን አንስተው፤ ፓርቲዎች አማራጭ ሀሳባቸውን ለማቅረብ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።
በኦሊያድ አህመድ