ስፓርት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

By Yonas Getnet

May 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 በማሸነፍ የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል።

የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ እስከ ሊጉ መጨረሻ ጨዋታ በነጥብ እኩል ሆነው ዛሬ በተገናኙበት ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው ረድኤት አስረሳኸኝ እና እሙሽ ዳንኤል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን 69 ያደረሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በዚህም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ለተከታታይ 6ኛ ጊዜ እና በአጠቃላይ ለ9 ጊዜ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል።

በሊጉ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫዋች ዳግማዊት ሰለሞን በ24 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆና አጠናቅቃለች።

በእንዳልካቸው ወዳጄ