አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረ ፎረም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
“በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የቀጣናው ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
መድረኩ ድንበር ተሻጋሪ የንግድና የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከርና የቀጣናውን ውስብስብ የሰላምና ደህንነት ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነስቷል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዘመናትን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት የነበረውን የቅንጅት ክፍተት በመስበር ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበና ትብብርን ማዕከል ያደረገ አዲስ የመፍትሄ አቅጣጫ መከተል አስፈላጊ መሆኑ በፎረሙ ላይ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር እሳቤ መሰረት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ ቀጣናዊ ውህደትን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በሚኪያስ አየለ