አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው የቀኝ መስመር የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ዳኒ ካርቫሃል ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያይቷል፡፡
የ34 ዓመቱ ተጫዋች በሪያል ማድሪድ ቆይታው 4 የስፔን ላሊጋ፣ 6 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና 2 የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎችን ጨምሮ 27 ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2013 ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን ሎስብላንኮሶቹን የተቀላቀለው ካርቫሃል ከአስደናቂ ስኬታማ ዓመታቶች በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር መለያየቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡