ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ የ131 ሰዎች ህይወት አለፈ ‎

By Hailemaryam Tegegn

May 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እየተስፋፋ በሚገኘው የኢቦላ ወረርሽኝ እስካሁን የ131 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ወረርሽኙ ባለፉት ሳምንታት በድጋሚ ከተቀሰቀሰ ወዲህ 513 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይገኛል፡፡

የኢቦላ ወረርሽኝ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተጨማሪ ወደ ኡጋንዳ መዛመቱና የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በሽታው በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል፡፡