አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የተጀመሩ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)።
ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎችን የማስተዋወቂያና የቅስቀሳ መርሐ ግብር በሀድያ ዞን በአመካ ወረዳ ጌጃ ከተማ አካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ ብልፅግና ከሕዝብ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ ይገኛል።
ፓርቲው በሁሉም የልማት መስኮች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ የክልሉ ሕዝብ የዚሁ ትሩፋት ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል።
በፓርቲው የተጀመሩ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ በበኩላቸው÷ ብልፅግና ፓርቲ የአብሮነትና የትብብር እሴቶችን በማጠናከር ለሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት መረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የፓርቲውን እሳቤ ተግባራዊ በማድረግ እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሕዝቡ ከፓርቲው ጎን በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንዲያጠናክር መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።