አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ሰላም ከማስፈን ሥራ ጎን ለጎን የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎች አከናውኗል አሉ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ።
በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የጎንደር ጊዜያዊ ዲሞብላይዜሽን ማዕከል ለቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሰላም ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መንግሥት ሁልጊዜ ለሰላም በሩ ክፍት ነው።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር ተመሰገን ጥላሁን በበኩላቸው÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሃድሶ ስልጠና ከ88 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።
ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ታጣቂዎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በአማራ ክልል በሁለት ዙር በ4 ማዕከሎች ከ15 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች በተሃድሶ ስልጠና እንዲያልፉ መደረጉን አንስተዋል።
የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በምናለ አየነው