ስፓርት

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ወደ ድል ተመለሰ

By Melaku Gedif

May 21, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ (2) እና ኤፍሬም ታምራት (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ተመልሷል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በዚሁ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከምድረ ገነት ሽረ ይገናኛሉ፡፡