አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂዷል።
መርሐ ግብሩ “በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
የምረጡኝ ቅስቀሳው በደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተሰላም፣ አዴት፣ ግንደወይን፣ ፈለገ ብርሃን፣ ደብረ ወርቅ ከተሞች እና ሌሎች አካባቢዎች መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብሩ ላይ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ተሳታፊ ወጣቶች በዚህ ወቅት የሀገርን ልማትና አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ አጋርነት የገለጹት ወጣቶቹ ÷ ለተጀመሩ የብልጽግና ጉዞዎች ስኬት የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም ተመልክቷል፡፡