የሀገር ውስጥ ዜና

በ700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ተመረቀ

By Abiy Getahun

May 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በ700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ተለዋጭ መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

7 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ተለዋጭ መንገዱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ በመሰረተ ልማት ሥራዎች ተጨባጭ ስኬት ተገኝተዋል።

ተለዋጭ መንገዱ ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የንግድ እንቅስቃሴ መጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም አንስተዋል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው÷ ተለዋጭ መንገዱ ለጅግጅጋ ከተማ የኢኮኖሚ አቅም፣ ውበትና እድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡ ያደርጋልም ብለዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ