ስፓርት

ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ

By Yonas Getnet

May 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ የ2025/26 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዓመቱ በ34 ጨዋታዎች 8 ግቦችን ሲያስቆጥር ÷ 20 ለግብ የሚሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን ደግሞ ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡