የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የጸረ ሠላም ኃይሎችን ድርጊት የማክሸፍ አቅም ገንብቷል – ፕሬዚዳንት ታዬ

By Mikias Ayele

May 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚነሱ የጸረ ሠላም ኃይሎችን ድርጊት የማክሸፍ አቅም ገንብቷል አሉ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ዕጩ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ዘመናዊ ትጥቆችን በመታጠቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ስኬታማ ተቋም ሆኗል።

በዚህም ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚነሱ የጸረ ሠላም ኃይሎችን ድርጊት ቀድሞ የማክሸፍ አቅም መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

አንጋፋው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በክህሎት የደረጀ ብቁ ሙያተኛ በማፍራትረገድ አይተኬ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ለጎረቤት ሀገራት ነጻ የትምህርት ዕድል መስጠቱ በጸጥታና ሠላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት እና የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፖሊስ ኃይሉ ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ በጠንካራ ዲሲፒሊን ሚናውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

በወንድሙ አዱኛ