ዓለምአቀፋዊ ዜና

አበረታች ሂደቶች የታዩበት የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር …

By Mikias Ayele

May 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፓኪስታን አሜሪካ እና ኢራንን ለመጨረሻ ጊዜ ለማሸማገል በቀረበው የድርድር ሀሳብ በሁለቱ ወገኖች በኩል ተስፋ ሰጭ ሂደቶች እየታዩ ነው አለች፡፡

ፓኪስታን ይህን ያለችው የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር አሜሪካ እና ኢራንን ለማሸማገል ያለመ የአንድ ቀን ጉብኝት በቴህራን ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

ጉብኝቱን አስመልከቶ የፓኪስታን ጦር ባወጣው መግለጫ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር በቴህራን ቆይታቸው ከኢራን ፕሬዚዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ እና ከከፍተኛ ተደራዳሪው ባገር ቃሊባፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ በተደረገው ውይይት ከአሜሪካ ጋር የመጨረሻ ድርድር ለማድረግ እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

የኢስላማባድ የሰላም ጥረት እና ግጭትን የማብረድ አንድ አካል በሆነው ውይይት ሀገራቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለማሸማገል በቀረበው የድርድር ሀሳብ አበረታች ሂደቶች መታየታቸውን ጦሩ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ÷ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን በሰላም ለመቋጨት የሚደረገው ድርድር መጠነኛ መሻሻሎች አሳይቷል ብለዋል።

ኢራን በበኩሏ ፓኪስታን በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ቀጣናዊ ቀውስ እንዲያበቃ እና የጦርነቱ ተሳታፊዎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ የምትጫዎተውን ገንቢሚና ማድነቋን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ