የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በግሉ ዘርፍ አበረታች ስራ እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Adimasu Aragawu

May 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በግሉ ዘርፍም አበረታች ስራ እየተሰራ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ ኒዩክለስ አጠቃላይ ሆስፒታል (Nucleus General Hospital) በህክምና ባለሙያዎች አክሲዮን ማህበር ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል ብለዋል።