አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂዷል።
መርሐ ግብሩ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
የምረጡኝ ቅስቀሳው በአሶሳ ዞን መንጌ ወረዳ፣ በመተከል ዞን ወምበራ እና ድባጤ ወረዳዎች እንዲሁም በካማሺ ዞን ካማሺ ከተማ መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብሩ ላይ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻው ተሳታፊዎች የሀገርን ልማትና አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ አጋርነት ገልጸው÷ ለተጀመሩ የብልጽግና ጉዞዎች ስኬት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የምርጫ ካርድ የወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፉም ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የምርጫ ምልክት እና የእጩ ትውውቅ አድርገዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ድጋሚ ከተመረጠ በክልሉ በፓርቲው መሪነት የተጀመሩ የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፓርቲው ተወካዮች አረጋግጠዋል፡፡