አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ሀገርን የማፅናት መልዕክት የተላለፈበት ነው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብሩ ብልጽግናን ከመደገፍ ባለፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማፅናት የጀግንነት አውድ ነው ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ “በምርጫ ብቻ” የሚለው ታላቅ መልዕክት ለዓለም መተላለፉን የገለጹት ከንቲባዋ፥ የከተማዋ ነዋሪዎች የሁልጊዜ መልዕክት ሀገር ማፅናት መሆኑን አውስተዋል፡፡
ዛሬ በማለዳ ወደ መስቀል አደባባይ በመትመም በሁነቱ ላይ ለተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡