የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ እየተከበረ ነው

By Mikias Ayele

May 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ሶላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ለማክበር የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል።

የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ መሀመድአሚን ተማም በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ህዝበ ሙስሊሙ ከሶላት በኋላ የአረፋ በዓል መገለጫ የሆነውን ስጦታ ለአቅመ ደካሞች መስጠት አለበት ብለዋል።

መደበኛ የሆነው መረዳዳት በማንኛውም ጊዜ ሊዘነጋ አይገባም ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በአብዱረህማን መሀመድ