አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በያቤሎ ከተማ የሚገኘውን የቦረና ባሕል ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
በ57 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ መሆኑን ገልጸው÷ በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ የቦረናን ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋልም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።