የሀገር ውስጥ ዜና

በየትኛውም የምርጫ ጣቢያ 200 ሜትር ርቀት ውስጥ ሆኖ ለመዘገብ ባጅ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡-

By Adimasu Aragawu

May 29, 2026

👉 የሀገሪቱን እና የአካባቢውን ባህልና ልምድ ማክበር፤

👉 በቦርዱ የተሰጠውን የመታወቂያ ባጅ በሚታይ መልኩ በመያዝ መንቀሳቀስ፤

👉 የመራጭ ምዝገባ መረጃዎችን በሰነድ ላይ ሲሰፍሩ ወይም መራጩ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የምርጫ ምልክት ሲያደርግ አለመቅረጽ ወይም ፎቶግራፍ አለማንሣት፤

👉 ግለሰቡ በግልጽ እየተቃወመው መራጮችን እና ሌላ ማንኛውንም ሰው ፎቶ ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል አለመቅረጽ እና ቃለ-መጠይቅ አለማድረግ፤

👉 የመራጮች ግላዊ ማንነትን በሚነካ አኳኃን መዝገብ፣ የመራጮችን ምዝገባ መታወቂያ ወይም ማንኛውንም ተመሳሳይ ሰነድ በፊልም አለመቅረጽ፣ ፎቶግራፍ አለማንሳት ወይም ኮፒ አለማድረግ፤

👉 የሕዝብን ሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ማክበር፤

👉 የቦርዱን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፀጥታና የደኅንነት እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት አካላትን ሚና እና ሥልጣን ማክበር፣

👉 ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስለ ኃላፊነታቸው ምክር ወይም መመሪያ አለመስጠት፣

👉 መራጩ ድምፁን ለማን እንደሰጠ አለመጠየቅ፣

👉 የሕግ ጉዳዮችን በራስ አለመተርጎም እና የምርጫ ሂደትን የሚመለከት ሕጋዊ ያልሆነ መረጃ ወይም መመሪያ አለማስተላለፍ፣

👉 ለድምፅ መስጫ የተከለለ ቦታ ካሜራም ሆነ ሌላ የድምፅ ወይም የምስል መቅጃ መሣሪያ አለመጠቀም፣

👉 ከአድሎና ከወገንተኝነት በፀዳ አኳኋን ተግባራትን ማከናወን ይጠቀሳሉ።