Fana: At a Speed of Life!

ለሀገሪቱ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ የተዘጋጁት የባሕር ዳር ነዋሪዎች…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ግንቦት 24 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን የሚበጀውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል አሉ፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፥ ዜጎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የጸና መንግስት ሊኖር ይገባል፡፡

ምርጫው ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ እንዲሆን የድርሻችንን እየተወጣን ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፥ የምርጫ ካርዳቸውን በወቅቱ በማውጣት የድምጽ መስጫውን እለት እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቀጣይነት ያለው ልማትና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እንዲሁም ለወጣቶች ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር በሕዝብ የተመረጠ መንግስት አስፈላጊ በመሆኑ በምርጫው በንቃት እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የፖሊሲ አማራጮች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው፥ የጥሞና ጊዜው የሚመርጡትን ፓርቲ ለመወሰን እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል፡፡

የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ድምጻቸው ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማትና ሰላም ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ በምርጫው በንቃት ሊሳተፉ ይገባል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.