የሀገር ውስጥ ዜና

በአሰላ የምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

By Adimasu Aragawu

May 29, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሰላ ምርጫ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ የማከፋፈል ስራ ተጀምሯል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል። ‎ ‎በዚህም ለምርጫው አስፈላጊ ዝግጅቶች በየምርጫ ክልሎቹ እየተካሄደ ይገኛል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአሰላ የምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጋላን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የምርጫ ቁሳቁስ በተገቢው ጥንቃቄ ለምርጫ ጣቢዎች እየተከፋፈለ ነው። ‎ ‎በአሰላ ምርጫ ክልል 108 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ገልጸው÷ ‎ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ‎ ‎በአብደላ አማን