የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

May 29, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቁሳቁስ የማጓጓዝ ሥራ እየተከናወነ ነው።

የክልሉ ሕዝብ ምርጫውን በባለቤትነት በመያዝ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አሚኮ ዘግቧል፡፡

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቆ እየተሰራጨ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡