አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24 ለሀገር የሚበጀውን ለመምረጥ ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቅን ነው አሉ የሀረር ከተማ ነዋሪዎች፡፡
ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉ ነዋሪዎች እንዳሉት÷ ምርጫ ለሀገር ሰላምና ልማት እንዲሁም ለዴሞክራሲ መጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
የዘንድሮውን ምርጫ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስኬታማ ለማድረግ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ምርጫ ሀገርን የመውደድ አንዱ የተግባር ማሳያ መሆኑን ገልጸው÷ በድምፅ መስጫ ዕለት ድምፃችንን ለመስጠትና ለሀገር ይበጃል ብለን ያመንበትን ለመምረጥ ቀኑን በጉጉት እየጠበቅን ነው ብለዋል፡፡
ምርጫው በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ የሚገኝ እድል በመሆኑ በድምፅ መስጫ ቀን ካርድ የወሰዱ ዜጎች ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራቸውን ፓርቲ መምረጥ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ