የሀገር ውስጥ ዜና

ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራንን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች

By Mikias Ayele

May 29, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራንን መንግሥት ለመምረጥ ዝግጁ ነን አሉ፡፡

ነዋሪዎቹ እንደገለፁት÷ በመጪው ሰኞ በሚካሄደው የድምጽ መስጠት ሂደት የመራጭነት ካርዳቸውን ተጠቅመው የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል።

በዕለቱም በምርጫ ጣቢያ ቀድመው በመገኘት ድምፃቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የአንድ ሰው ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ ዜጎች በዕለቱ ድምፃቸውን በመስጠት የዜግነት ግዴታውቸን እንዲወጡም አስገንዝበዋል።

ምርጫው ነጻ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።