የሀገር ውስጥ ዜና

ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ – ኢጋድ

By Mikias Ayele

May 29, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡

ምርጫው ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል።

ኢጋድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷ የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት የምርጫ ትብብር ጋር በመሆን የምርጫውን ሂደትን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በውይይቱ የሲቪል ማህበረሰቦች የዴሞክራሲ ሂደቶችን፣ የምርጫ ዝግጅት እና የአካባቢ ምርጫን በመታዘብ ረገድ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ምክክር መደረጉን አንስቷል፡፡

ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች የሲቪክ ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ መነሳቱን ተጠቅሷል፡፡

ውይይቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ እንዲኖር የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አካል መሆኑንም አስታውቋል፡፡