ስፓርት

መቐለ 70 እንደርታ እና ባሕር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

By Yonas Getnet

May 30, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ እና ባሕር ዳር ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገው የመቐለ 70 እንደርታ እና የባሕር ዳር ከተማ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መድን ጨዋታ ደግሞ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ቀደም ሲል በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 እንዲሁም ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።