የሀገር ውስጥ ዜና

በምርጫ ካርዳችን ለሀገርና ሕዝብ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ በጉጉት እየጠበቅን ነው – የባቱና አሰላ ከተማ ነዋሪዎች

By Yonas Getnet

May 30, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ‎የሚወክለንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ቀኑን በጉጉት እየጠበቅን ነው አሉ የባቱ እና አሰላ ከተማ ነዋሪዎች። ‎ ነዋሪዎቹ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን ነፃነትና መልካም ስም ከማስፈን አንጻር ትልቅ ሚና አለው፡፡ ‎ ‎የሚወክለንን ፓርቲ የምንመርጥበትን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ‎ለሀገር ግንባታና ዴሞክራሲ የአንድ ሰው ድምፅ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

‎ሀገርን የሚጠቅምና የሚገነባ እንዲሁም የዜጎችን ሕይወት ያሻሽላል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ‎ ‎ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በ‎አብደላ አማን