አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምርጫው ዕለት ለሀገር ልማት ይበጃል የምንለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል አሉ የሐረር እና ቆቦ ከተማ ነዋሪዎች፡፡
የሐረር ከተማ ወጣቶች በምርጫው ዕለት ለሀገር ልማት ይበጃል የምንለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንና በምርጫ ካርዳቸው መንግሥት የመመሥረት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል።
ሕዝብ በምርጫ ካርድ መንግሥት የመመስረት ዴሞክራሲያዊ መብቱን ሊጠቀም እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በቀጣይ ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅመውን ፓርቲ ለመምረጥ ምርጫው መሠረታዊ እንደሆነ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።