የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገርን ይመራል ብለን የምናምንበትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የባቹማ ከተማ ነዋሪዎች

By Mikias Ayele

May 31, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የባቹማ ከተማ ነዋሪዎች ሀገርን ይመራል ብለን የምናምንበትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል አሉ።

ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት፤ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ በነቂስ ወጥተው ለመምረጭ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም ሀገር ይመራል ብለው ያመኑትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን  ተናግረዋል።

በመሆኑም ነገ በሚካሄደው ምርጫ በወሰዱት ካርድ ድምፃቸውን በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።