የሀገር ውስጥ ዜና

በባቲ ከተማ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

May 31, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ የምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

በተጨማሪም መራጮች ያለምንም እንግልት መምረጥ እንዲችሉ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለህዝቡ ምቹ የሆነ የጊዜያዊ መጠለያ መዘጋጀቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡