አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ይገኛል።
በነገው ዕለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረትም በአስተዳደሩ የምርጫ ቁሳቁስ ከትናንት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ ያሲን መሐመድ፤ የምርጫ ቁሳቁስ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ በየምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶቹ ተደራሽ ይሆናሉ ብለዋል።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል
#Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision