አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሒደት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሒደት ዙሪያ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በቅድመ ምርጫ ሒደት፣ ስለ ምርጫ ታዛቢዎች ስምሪት እንዲሁም ታዛቢ ቡድኖች ተቀናጅተው መስራት በሚችሉባቸው ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች የምርጫው ሒደት ሰላማዊ፣ ተዓማኒ ግልጽና አካታች እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡