አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ክልሎች ዜጎች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል፡፡
ሕዝቡ ከማለዳ ጀምሮ በነቂስ በመውጣት በምርጫው ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን፥ የድምጽ መስጠት ሒደቱ የምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች በምርጫው ድምጻቸውን ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን፥ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፡፡
10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም 80 የግል እጩዎች ቀርበዋል፡፡