የሀገር ውስጥ ዜና

50 ሺህ 188 የምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተከፍተዋል – ቦርዱ

By Melaku Gedif

June 01, 2026

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 50 ሺህ 188 የምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተከፍተው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጀምሯል አለ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የምርጫውን ጊዜያው ሂደት በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ 50 ሺህ 188 የምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተከፍተው ድምጽ ሰጪዎችን እያስተናገዱ ነው፡፡

እንዲሁም 695 ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸውን ጠቅሰው፤ 4 የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በጸጥታ ምክንያት ተቋርጠዋል ብለዋል።

በዲጂታል የተመዘገቡ መራጮቾ የገፅ ቁጥር ባለመገኘቱ ረጃጅም ሰልፎች መኖራቸውን አንስተው ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መራጮች ከማለዳ ጀምሮ በነቂስ ወጥተው ድምፅ እየሰጡ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በቤተልሔም መኳንንት

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision