አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ሕገ መንግሥታዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሚፈልጉት ፓርቲ ድምጽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደት ድምጽ መስጠት የሀገርን መጻኢ ዕድል ለመወሰን እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የሚያስችል መሠረታዊ መብት መሆኑን አስታውሰዋል።
መብታቸውን በመጠቀም ለሀገር ይበጃል ያሉትን ዕጩ በነፃነት መምረጣቸውን ገልጸው፤ ሀገራችን የምትፈልገው በሰላማዊ መንገድ የተመረጠ መሪ ነውም ብለዋል።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision